የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶስዬሽን የረዥም ጊዜ አጋር የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነሓሴ 27 ቀን በአዲሱ ዋና መ/ቤት ህንጻ ውስጥ በዓይነቱ ልዩ እና ሙሉ ለሙሉ ዲጂታል (paperless) የሆነ የኮርፖሬት ደንበኞች አገልግሎት ቅርንጫፍ አስመርቋል፡፡ በዚህ ስነስርዓት ላይ አሶስዬሽኑን በመወከል ፕረዚዳንቱ ዶ/ር አምዲሳ ተሾመ ተገኝተዋል፡፡በስነስርዓቱ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሺዲ ናቸው፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ የተዘጋጀውን ሪበን ከቆረጡ እና የቅርንጫፉን ስያሜ (አቢይ ቅርንጫፍ) የጋረደውን መጋረጃ ከገለጡ በኋላ ቅርንጫፉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተጎበኝቷል፡፡ ከጉብኝቱ በኋላ ታዳሚዎቹ ( ኮርፖሬት ደንበኞቹ) ወደ ዋናው አዳራሽ በመግባት የባንኩን የ80 ዓመት ጉዞ ሚያሳይ አጭር ዘጋቢ ፊልም ተመልክተዋል፡፡ ቀጥሎም ባንኩ ያደረገውን የሁለት ዓመት የለውጥ ጉዞ (transformation) በምስል የተደገፍ ገለፃ ተደርጓል፡፡በመጨረሻም የአሶሴሽኑ ፕረዚዳንት ለኮርፖሬት ደንበኞች በተዘጋጀው የክብር መዝገብ ላይ ባንኩ ማህበራችንን በማክበር በዚህ ታላቅ በዓል ላይ እንድንገኝ በመጋበዙ አመስግነዋል፡፡
Focusing on research undertakings related to economic growth and
development, inflation and unemployment, savings and investment, government spending,