For Trainings, Membership and EEA Publications follow us on Telegram: https://t.me/econ_association የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶስዬሽን እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግንኙነት መገለጫ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶስዬሽን እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግንኙነት መገለጫ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶስዬሽን የረዥም ጊዜ አጋር የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነሓሴ 27 ቀን በአዲሱ ዋና መ/ቤት ህንጻ ውስጥ በዓይነቱ ልዩ እና ሙሉ ለሙሉ ዲጂታል (paperless) የሆነ የኮርፖሬት ደንበኞች አገልግሎት ቅርንጫፍ አስመርቋል፡፡ በዚህ ስነስርዓት ላይ አሶስዬሽኑን በመወከል ፕረዚዳንቱ ዶ/ር አምዲሳ ተሾመ ተገኝተዋል፡፡በስነስርዓቱ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሺዲ ናቸው፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ የተዘጋጀውን ሪበን ከቆረጡ እና የቅርንጫፉን ስያሜ (አቢይ ቅርንጫፍ) የጋረደውን መጋረጃ ከገለጡ በኋላ ቅርንጫፉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተጎበኝቷል፡፡ ከጉብኝቱ በኋላ ታዳሚዎቹ ( ኮርፖሬት ደንበኞቹ) ወደ ዋናው አዳራሽ በመግባት የባንኩን የ80 ዓመት ጉዞ ሚያሳይ አጭር ዘጋቢ ፊልም ተመልክተዋል፡፡ ቀጥሎም ባንኩ ያደረገውን የሁለት ዓመት የለውጥ ጉዞ (transformation) በምስል የተደገፍ ገለፃ ተደርጓል፡፡በመጨረሻም የአሶሴሽኑ ፕረዚዳንት ለኮርፖሬት ደንበኞች በተዘጋጀው የክብር መዝገብ ላይ ባንኩ ማህበራችንን በማክበር በዚህ ታላቅ በዓል ላይ እንድንገኝ በመጋበዙ አመስግነዋል፡፡

Leave a Reply

Ethiopian Economics Association

Ask any information related to membership inquiries.

Hello, Welcome to the site. Please click below button for any membership inquiries.

×