2. @tikvahethmagazine ባንኩ በበጀት ዓመቱ 3.8 ቢልዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከፍተኛ የፖሊሲ ፎረም በማከናወን ላይ ይገኛል።
በዚሁ ፎረም ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮሐንስ በተለይም ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ባንኩ በ2013 ዓ.ም 4.2 ቢልዮን ብር ማትረፉን አስታውሰው በዘንድሮው አመትም 3.8 ቢልዮን ብር ከታክስ በፊት ትርፍ ማግኘቱን ነው የጠቆሙት።
በተጨማሪም ባንኩ በያዝነው ዓመት 19 ቢልዮን ብር ለማበደር አቅዶ 22 ቢልዮን ብር ያበደረ ሲሆን ይህም ከዕቅዱ 120% ምሳደጉን ገልፀው በ2015 በጀት ዓመትም 30 ቢልዮን ብር ለማበደር መታቀዱን አያይዘው ተናግረዋል።
ባንኩ በቱሪዝም፣ በግብርና እና ሌሎችም ዘርፎች በትኩረት እየሰራ መሆኑን ያስታወቁት ፕሬዝዳንቱ ለ33,000 ወጣቶችም በአነስተኛና መካከለኛ ስልጠና መሰጠቱን አንስተዋል።
በመጨረሻም 78 ቅርንፎች ያሉት ባንኩ በቀጣይ 30 ቅርንጫፎችን በመክፈት ወደ 108 በማሳደግ በ22 ዲስትሪክት ተቀዛቅዘው ያሉትን በማጠናከር በትከረት ለመስራት መዘጋጀታቸውን ጨምረው ገልፀዋል።
@tikvahethmagazine
3. #ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተለያዩ ጥናት አድራጊዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ፖለቲከኞች በተገኙበት ለ2 ቀናት የቆየ ከፍተኛ የፖሊሲ ፎረም አካሂዷል።
በፎረሙም በ4 ዋና ጉዳዮች ላይ የትዘጋጁ ጥናቶች ለውይይት ቀርበዋል።
ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠረው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጂዲፒውን በ1% ሊቀንስ እንደሚችልና 71 ሚልዮን የሚጠጋው ህዝብ ደግሞ በዋጋ ግሽበት የተነሳ ከድህነት ወለል በታች ሊገባ እንደሚችል ተገምቷል።
ሀገራችን ኢትዮጵያም 33% የዋጋ ግሽበት ያስተናገደች ሲሆን ከዚህም ውስጥ 13% ሚሆነው በጦርነቱ ምክንያት የመጣ መሆኑ በተደረጉ ጥናቶቾ ተመላክቷል።
በሀገሪቷም ተጨማሪ 3 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች ከድህነት ወለል በታች ሊገቡ እንደሚችሉና ጂዲፒያችንም ወደ 7% ሊቀንስ ይችላል ነው የተባለው።
ከ40% በላይ ከሁለቱ ሀገራት ምርቶች የምታስገባው ኢትዮጵያ ነዳጅ፣ ማዳበሪያና ምግብ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥሮባታል፤ የኮሮና ወረርሽኝ፣ በሀገሪቱ የተከፈተው ጦርነት ፣ የተለያዩ ብድሮች፣ በተፈጥሮ አደጋዎችና ሌሎች ምክንያቶች ግሽበቱን በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደቻለ ተገልጿል።
ለዚህ ሁሉ ችግር ምርታማነትን ማሳደግ፣ የነዳጅ አጠቃቀማችንን ማስተካከል ቢቻል መቆጠብ፣ ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ማምረት፣ የአረንጓዴ ኋይልን ማጠናከር፣ ግጭትን ማስቆምና ሌሎችም እንደ መፍትሔ ተጠቁመዋል።
የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በመስራት ለውይይት የሚያቀርበው ማኅበሩ ባለፈው ዓመት 10 ጥናቶችን ያቀረበ ሲሆን ሌሎች የምርምር ስራዎችንም እንደሚያቀርብ አስታውቆ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በጋራ እየሰራ ያለ ገለልተኛ ተቋም መሆኑን ገልጿል።
@tikvahethiopia
4. https://youtu.be/MvVHVK3448U
5. https://www.ethiopianreporter.com/110211/
7. https://www.ena.et/?p=183251
8. https://www.youtube.com/watch?v=mYpxXg4napU
9. @tikvahethmagazine, @tikvahethiopia
10. https://www.youtube.com/watch?v=4XRROXIiP5Q
11.
Expertise view on the effect on economic sanctions and policy options
Expertise view on financial liberalization in Ethiopia
Expertise view on the economic consequences of the Russia-Ukraine conflict on Ethiopia’s Economy