የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን በኮምኒኬሽን እና በሚዲያ ግንኙነት ዙሪያ ለሰራተኞቹ እና ለአባላቱ ስልጠና ሰጠ።

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክ አሶሴሽን ከዪኤስኤድ/ ኦቲአይ (USAID/OTI) ጋር በመተባበር ለሰራተኞቹ እና ለአባላቱ የሶስት ቀን ስልጠናን አከናውኗል። ስልጠናው በኮምኒኬሽን፣ የሚዲያ ግንኙነት እና የድርጅቱን ስራዎች የማስተዋወቂያ መንገዶች ላይ ያተኮረ ሲሆን ዋና አላማውም ማህበሩ የምርምር ስራዎችን፣ የፓሊሲ ፎረም ዝግጅቶችን እና ሌሎች ስራዎቹን በሚገባ ለማስተዋወቅ የሚያስችለውን አቅም መጨመር ነው።

ስልጠናው የሚዲያ፣ የኮምኒኬሽን እና የካምፔይን አማካሪ በሆኑት በሶልያና ሽመልስ የተሰጠ ሲሆን 21 የድርጅቱ ሰራተኞች፣ አባላት እና አጋሮች ተገኝተዋል።

Leave a Reply