For Trainings, Membership and EEA Publications follow us on Telegram: https://t.me/econ_association EEA Honored with Prestigious Award!

EEA Honored with Prestigious Award!

The Ethiopian Economics Association (EEA) is delighted to announce that it has been bestowed
the highest honor by the Abyssinia Industry Award.

In addition to the association’s Gold trophy and Diploma of Honor, twelve exemplary employees,
including team leaders, administrative staff, and mid-level management, were awarded gold
medals and diplomas. The association’s CEO, Professor Mengistu Ketema, was honored with a
gold cordon and diploma.

Established 33 years ago, the Abyssinia Industry Award is an independent institution renowned
for recognizing outstanding organizations in Ethiopia. The EEA was selected for its exceptional
contributions to research, scientific events, publications, capacity building, and policy advice.

This distinguished recognition is a testament to the unwavering dedication and tireless efforts of
current and previous Executive Committee Members led by nine Presidents, management
members, and staff since our founding in 1991. We owe a profound debt of gratitude to our
visionary founders and subsequent leaders for their steadfast commitment.

We extend our sincere appreciation to all past and present Executive Committee members for
their selfless service and unwavering support. Their dedication, rendered without conflict of
interest, has been instrumental to our success. We also express our heartfelt thanks to all EEA
members and partners for their continuous support and encouragement.
The EEA is committed to accelerating its momentum and continuing its mission with renewed
vigor.

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሸን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ተበረከተለት!
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሸን በአቢሲኒያ ኢንደስትሪ ሽልማት ድርጅት ከፍተኛውን ሽልማት ማግኘቱን ሲገልጽ በደስታ
ነው። ይህ ልዩ እውቅና ላለፉት 33 ዓመታት ሰራተኞቻችን፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና ዘጠኝ ፕሬዚዳንቶች
ያላሰለሰ ጥረት የሚያሳይ ነው።

ከማህበሩ አጠቃላይ ሽልማት በተጨማሪ የቡድን መሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና መካከለኛ አመራሮችን ጨምሮ 12
አርአያ ለሆኑ ሰራተኞች የወርቅ ሜዳሊያ፥ ኒሻን እና ዲፕሎማ ተሰጥቷቸዋል። ለአሶሴሸን ከተበረከተዉ የወርቅ ዋንጫ
እና የክብር ዲፐሎማ በተጨማሪ የማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕ/ር መንግስቱ ከተማ የወርቅ ኮርዶን እና ዲፕሎማ
ተሸልመዋል።

ከ30 ዓመታት በፊት የተቋቋመው የአቢሲኒያ ኢንዱስትሪ ሽልማት በኢትዮጵያ ላሉ ድርጅቶች እውቅና በመስጠት
የሚታወቅ ራሱን የቻለ ተቋም ነው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሸን የተመረጠው በምርምር፣ ሳይንሳዊ የዉይይት
መድረኮችን በማዘጋጀት፣ ሕትመቶችን በማሳተም እና በማሰራጨት፣ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት እና የፖሊሲ
ምክረ ሀሳቦችን በማቅረብ ላበረከተው ልዩ አስተዋጽዖ ነው። ይህ ስኬት አሶሴሸኑ ከተመሠረተበት ከ1983 ዓ.ም
ጀምሮ አባሎቻችን፣ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎቻችን፣ አመራሮቻችን እና ሰራተኞቻችን የጋራ ድምር ዉጤት ነው። ባለራዕይ
መስራቾቻችን እና በተክታታይ አሶሴሸኑን የመሩ የስራ አስፈጻሚ አባላትን በሙሉ ላሳዩት ጽኑ ቁርጠኝነት ትልቅ ምስጋና
እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሸን በተጓዘባቸዉ አመታት በሙሉ ከራስ ወዳድነት በጸዳ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት
ላበረከቱ እና በማበረከት ላይ ላሉ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እና የማያወላውል ድጋፍ ላደረጉልን የማህበሩ አባላት
እና አጋሮች በሙሉ ልዩ ልባዊ አድናቆት እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሸን አገልግሎቱን በማስፋት እና ተልዕኮውን በአዲስ ጉልበት ለመቀጠል ቁርጠኛ ነው!

Abisiniya Award

Leave a Reply

Ethiopian Economics Association

Ask any information related to membership inquiries.

Hello, Welcome to the site. Please click below button for any membership inquiries.

×